የኢራን፣ ቻይና እና ሩሲያ ጥምር ወታደራዊ ልምምድ ግብ የምዕራባውያንን የበላይነት ማስቆም ነው ሲሉ ባለሙያው ተናገሩ በቅርቡ በቻይና፣ ሩሲያ እና ኢራን መካከል በኢራን የባሕር ጠረፍ የተካሄደው የሴኪዩሪቲ ቤልት 2025 የጋራ ወታደራዊ ልምምድ የጂኦፖለቲካል ታዛቢዎችን ትኩረት በከፍተኛው ስቧል። "ከጂኦፖለቲካዊ እይታ አንፃር ኢራን፣ ቻይና እና ሩሲያ ያደረጉት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ የሶስቱ ሀገራት ስትራቴጂያዊ አጋርነት እያደገ መምጣቱን ያሳያል" ሲሉ በዚምባብዌ ቢንዱራ የሳይንስ ትምህርት ዩኒቨርስቲ የሰላምና አስተዳደር ክፍል መምህር ዶ/ር ዳርሊንግተን ንጎኒ ማሁኩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የሴኪዩሪቲ ቤልት 2025 ልምምድ "በምዕራባውያን በበላይነት ከተያዙ ተቋማት በመላቀቅ ለቀጣናዊ አንድነት እና መረጋጋት አዲስ መንገድ ለማበጀትና አማራጭ የኃይል እና የጸጥታ ማዕቀፎችን ለመፍጠር ፍላጎት እንዳለ ያሳያል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል። “የጋራ ልምምዱ ሩሲያ፣ ቻይና እና ኢራን ትብብራቸውን ለማጠናከር፤ በምላሹም የምዕራቡን ዓለም የበላይነት እና ፈላጭ ቆራጭነት ለማስቀጠል አላግባብ ጥቅም ላይ የዋለውን ኔቶን ለማስቆም መዘጋጀታቸውን ያሳያል" ሲሉ ዶ/ር ማሁኩ ተናግረዋል። ልምምዱ ምዕራባውያን ሀገራት የዓለም ፖለቲካን እንደፈለጉ መቆጣጠር እንደማይችሉ መልዕክት ከማስተላለፉ ባሻገር፤ "ከሩሲያና ቻይና ጋር በመተባበር ታዳጊ ኃያላን አሁን ተጽእኗቸውን እያሳደሩ መምጣታቸውን ያመለክታል" ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የኢራን፣ ቻይና እና ሩሲያ ጥምር ወታደራዊ ልምምድ ግብ የምዕራባውያንን የበላይነት ማስቆም ነው ሲሉ ባለሙያው ተናገሩ
የኢራን፣ ቻይና እና ሩሲያ ጥምር ወታደራዊ ልምምድ ግብ የምዕራባውያንን የበላይነት ማስቆም ነው ሲሉ ባለሙያው ተናገሩ
Sputnik አፍሪካ
የኢራን፣ ቻይና እና ሩሲያ ጥምር ወታደራዊ ልምምድ ግብ የምዕራባውያንን የበላይነት ማስቆም ነው ሲሉ ባለሙያው ተናገሩ በቅርቡ በቻይና፣ ሩሲያ እና ኢራን መካከል በኢራን የባሕር ጠረፍ የተካሄደው የሴኪዩሪቲ ቤልት 2025 የጋራ ወታደራዊ ልምምድ... 15.03.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-03-15T21:03+0300
2025-03-15T21:03+0300
2025-03-15T21:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የኢራን፣ ቻይና እና ሩሲያ ጥምር ወታደራዊ ልምምድ ግብ የምዕራባውያንን የበላይነት ማስቆም ነው ሲሉ ባለሙያው ተናገሩ
21:03 15.03.2025 (የተሻሻለ: 21:44 15.03.2025)
ሰብስክራይብ