"የመጪው ዘመን የዲጂታል ኢንዱስትሪ እየተገነባ ነው፤ የዚህ ሂደት አርክቴክት ከሆኑት ውስጥ ሩሲያ አንዷ እየሆነች ነው"

ሰብስክራይብ
"የመጪው ዘመን የዲጂታል ኢንዱስትሪ እየተገነባ ነው፤ የዚህ ሂደት አርክቴክት ከሆኑት ውስጥ ሩሲያ አንዷ እየሆነች ነው" ይህን ያሉት በሞሮኮ በሚካሄደው ጂቴክስ አፍሪካ 2025 የዲጂታል ኤግዚቢሽን የሚሳተፈውን የሩሲያ የንግድ ልዑክ የወከሉት አሌክሲ አንድሬቭ ናቸው። "ለአፍሪካ ሀገራት ከሶፍትዌር ምርቶች በተጨማሪ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት እና እድገት ማረጋገጥ የሚያስችል የዲጂታል መፍትሄ ሥነ-ምህዳር እናቀርባለን" ሲሉ አሌክሲ አንድሬቭ ተናግረዋል። በአጠቃላይ 50 የሚጠጉ የሩሲያ ኩባንያዎች በዝግጅቱ ላይ የሚሳተፉ ሲሆን ከሚያቀርቧቸው አገልግሎቶች ውስጥ ከታች የተዘረዘሩት ይጠቀሳሉ፦  የፈጠራ መሣሪያዎች፣ ሶፍትዌር፣ ምናባዊ እውነታ ማስመሰያዎች፣ የዲጂታል ሲቲ መፍትሄዎች፣ የዲጂታል መድኃኒት መፍትሄዎች። ኤግዚቢሽኑ ከሚያዝያ ሚያዝያ 6 እስከ 8 2017 ዓ.ም በማራኬሽ ይካሄዳል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0