ኢትዮጵያ የምትታወቅበት የአረቢካ ቡና ዋጋ በዓለም ዓቀፍ ገበያ 20 በመቶ ጨመረ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የምትታወቅበት የአረቢካ ቡና ዋጋ በዓለም ዓቀፍ ገበያ 20 በመቶ ጨመረ የተባበሩት መንግሥታት የምግብና እርሻ ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው፤ ኢትዮጵያ የምትታወቅበት የአረቢካ ቡና ዋጋ ባለፈው ዓመት በዓለም አቀፍ የንግድ ልውውጥ 70 በመቶ ጨምሮ ነበር። የአረቢካ ቡና ዋጋ በዚህ ዓመት ከ20 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል የተባለ ሲሆን ለዚህም የአቅርቦት እጥረት እና የዓለም አቀፍ ክምችት መቀነስ በምክንያትነት ተነስተዋል። የቡና ፍሬ አምራቾች ዋጋ በኢትዮጵያ 17.8 በመቶ፣ በኬንያ 12.3 በመቶ፣ በብራዚል 13.6 በመቶ እና በኮሎምቢያ 11.9 በመቶ እንደጨመረ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገልጿል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0