አሜሪካ እና እስራኤል ከጋዛ የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያንን ወደ ሌላ ቦታ ለማዛወር  ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ሶማሊላንድንን እንዳነጋገሩ ተዘገበ

ሰብስክራይብ
አሜሪካ እና እስራኤል ከጋዛ የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያንን ወደ ሌላ ቦታ ለማዛወር  ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ሶማሊላንድንን እንዳነጋገሩ ተዘገበ ሱዳን ሃሳቡን ውድቅ እንዳደረገች የተገለፀ ሲሆን የሶማሊያ እና ሶማሊላንድ ባለስልጣናት በበኩላቸው ስለ ጉዳዩ እንደማያውቁ ተናግረዋል ተብሏል። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፍልስጤማውያንን የማፈናቀል እቅዳቸውን ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ፤ በእስራኤል መሪነት ጥያቄው እንደቀረበ ስማቸው ያልተገለጸ የአሜሪካ እና የእስራኤል ባለስልጣናት አረጋግጠዋል ሲሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በ "ፍቃደኝነት" ላይ የተመሠረተ የፍልስጤማውያን ስደትን የሚደግፉት የእስራኤል የገንዘብ ሚኒስትር ቤዛሌል ስሞትሪች፤ ማስተናገድ የሚችሉ ሀገራት ልየታና በመከላከያ ሚኒስቴር ሥር ራሱን የቻለ የኢሚግሬሽን ቅርንጫፍ ለማቋቋም ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ገልፀዋል። የትራምፕ እቅድ ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ጋዛውያንን በዘላቂነት በማፈናቀል አሜሪካ ግዛቱን ተቆጣጥራ እንደምታለማ ይገልጻል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ሃሳቡን “ድንቅ ራዕይ” ብለውታል። የአረብ ሀገራት እና ፍልስጤማውያን ሃሳቡን አጥብቀው ቢቃወሙትም ኋይት ሀውስ ግን ትራምፕ "በእቅዳቸው እንደጸኑ" አስታውቋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0