ሩሲያ በተወሰኑ የአፍሪካ ሀገራት የምትልከውን የስንዴ ምርት መጠን በእጥፍ ጨመረች

ሰብስክራይብ
ሩሲያ በተወሰኑ የአፍሪካ ሀገራት የምትልከውን የስንዴ ምርት መጠን በእጥፍ ጨመረች እ.አ.አ በ2024 ተመሳሳይ ጊዜ ወደ ሞሮኮ ከተላከው የስንዴ ምርት ጋር ሲነፃፀር በዚህ ዓመት የተላከው 124 ሺህ ቶን ምርት የ2.3 እጥፍ ጭማሪ አለው። ወደ ናይጄሪያ የተላከው ምርት በ2.7 እጥፍ በመጨመር ከ48 ሺህ 900 ቶን ወደ 131 ሺህ 400 ቶን አድጓል። ወደ ካሜሩን የተላከው በ2.2 እጥፍ በመጨመር ከ23 ሺህ 200 ቶን ወደ 50 ሺህ ቶን ከፍ ብሏል፡፡እድገቱ የተመዘገበው ከ2025 መጀመርያ እስከ መጋቢት 9 ባለው ግዜ ውስጥ መሆኑን የሩሲያ ፌደራል አገልግሎት የእንስሳት ህክምና እና የእህል ቁጥጥር ተቋም መረጃ ያሳያል።ሩሲያ ወደ አፍሪካ የምትልከው ቀዳሚ የግብርና ምርት እህል ነው። እ.አ.አ በ2024 ከተላኩት የግብርና ምርቶች ውስጥ 87 በመቶው የሚሆነውን አጠቃላይ የዋጋ ድርሻ ይሸፍናል።ሩሲያ ባለፈው ዓመት ከ7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን የግብርና ሸቀጦችን ወደ አፍሪካ የላከች ሲሆን ከ2023 ጋር ሲነፃፀር 19 በመቶ ጨምሯል። ሩሲያ የግብርና ምርቶቿን ለ45 የአፍሪካ ሀገራት ልካለች።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0