ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ መያዝ አለባት አሉ

ሰብስክራይብ
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ መያዝ አለባት አሉበአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የስልጣን ርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዓለም የውሳኔ ስጪ መድረኮች ላይ የአፍሪካ ተሳትፎ  አስፈላጊ እና ወሳኝ እንደሆነ አበክረው ተናግረዋል።አፍሪካ በዓለም አቀፉ መድረክ ላይ ያላትን ትክክለኛ ቦታ ለማረጋገጥ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ መቀጠል እንዳለባት ገልጸዋል።ኢትዮጵያ ለዚህ ጥረት ድጋፍ መስጠቷን እንደምትቀጥል ቃል የገቡት ፕሬዝዳንቱ፤ ለአዲሱ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን አመራር ስኬታማነት የድርሻዋን እንደምትወጣም አረጋግጠዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0