የኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ መከላከያ ተቋማት በተለያዩ ወታደራዊ መስኮች ዙሪያ በትብብር ለመሥራት ተስማሙ

ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ መከላከያ ተቋማት በተለያዩ ወታደራዊ መስኮች ዙሪያ በትብብር ለመሥራት ተስማሙስምምነቱ የኢትዮጵያና የሩዋንዳ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሞች በተለያዩ ወታደራዊ መስኮች በጋራ መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከተወያዩ በኋላ የመጣ እንደሆነ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አስታውቋል፡፡ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የሩዋንዳው አቻቸው ጄነራል ሙባረክ ሙጋጋ ፈርመዋል። ሁለቱ ሀገራት በወታደራዊ አቅም ግንባታ ስልጠና፣ በተሞክሮ ልውውጥ፣ ሽብርተኝነትን በመከላከል እና በሌሎችም ተያያዥነት ባላቸው ወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ከስምምነት ላይ እንደደረሱ ተነግሯል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0