የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ክልሉ ወደ አላስፈላጊ ትርምስና ጦርነት እንዳይገባ ሁሉም የበኩሉን እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ

ሰብስክራይብ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ክልሉ ወደ አላስፈላጊ ትርምስና ጦርነት እንዳይገባ ሁሉም የበኩሉን እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ዛሬ በአዲስ አበባ በሰጡት ማብራሪያ ትግራይ ክልልን ወደ አላስፈላጊ ትርምስና ጦርነት ለመክተት የሚሞክረው በክልሉ የሕግ ተቀባይነት ያጣው የሕወሓት አንጃ ነው ብለዋል። አንጃው በቀበሌ፣ ወረዳ እና ዞን ባሉ ተቋማት ማሕተሞችን በሕገ-ወጥ መንገድ እየነጠቀ እንደሚገኝ አመልክተዋል። ሆኖም ግዜያዊ አስተዳደሩ እስካሁን የፌደራል መንግሥትን ጣልቃ ገብነት እንዳልጠየቀ ገልጸዋል። ጊዜያዊ አስተዳዳሪው ትግራይ ክልል ዳግም ወደ ጦርነት እንዳይመለስ የፌደራል መንግሥት የሚጠበቅበትን ሊወጣ ይገባልም ብለዋል። የትግራይ ክልልን ወደ አላስፈላጊ ትርምስና ጦርነት ለመክተት የሚደረገውን ሙከራ ለማስቆም የክልሉ ሕዝብ፣ የፌደራል መንግሥትና ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0