የአፍሪካ ሀገራት ራስን ለመቻል እና ፈጠራ ላይ የሚያደርጉትን ጥረት ሊያጠናክሩ ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ ጥሪ አቀረቡ

ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሀገራት ራስን ለመቻል እና ፈጠራ ላይ የሚያደርጉትን ጥረት ሊያጠናክሩ ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ ጥሪ አቀረቡበ57ኛው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የአፍሪካ የገንዘብ፣ የፕላን እና ኢኮኖሚ ሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ ሰመረታ ሰዋሰው የፋይናንስ እጥረት የአፍሪካን የእድገት አቅም እንደገደበ ተናግረዋል።ሚኒስትር ደኤታዋ አክለውም ዓለም ሽግግር ላይ እንደምትገኝ እና የልማት ድጋፎች እየቀነሱ መምጣታችውን አንስተው፤ የአፍሪካ ሀገራት ራሳቸውን ለመቻል እና በፈጠራ ላይ የሚያደረጉትን ጥረት ሊጠናክሩ ይገባል ብለዋል። “ዓለም በስርዓት ሽግግር እያለፈች እና የልማት ድጋፍ እየቀነሰ ባለበት ወቅት፤ ይህ ለእኛ አስቸኳይ ፈተና እና አጀንዳ ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0