የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ለአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ሙሉ ትግበራ ጥሪ አቀረበ

ሰብስክራይብ
የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ለአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ሙሉ ትግበራ ጥሪ አቀረበ ጥሪው የተደረገው ዛሬ በአዲስ አበባ በተጀመረው 57ኛው የአፍሪካ ሀገራት የፋይናንስ፣ የፕላንና የኢኮኖሚ ሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ነው። በጉባኤው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ምክትል ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ፔድሮ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት በተሟላ መልኩ እንዲተገበር ጥሪ አቅርበዋል። "የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና አህጉራዊ ስምምነት ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ እድገት ገዥ መመሪያ እና አፍሪካውያን የጋራ አቋም የሚያበጁበት ትልቅ የፖለቲካ መድረክ ነው" ሲሉ ምክትል ዋና ጸሃፊው አክለዋል። የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ስምምነቱን በተሟላ መልኩ በመተግበር እና ማነቆዎችን በማስወገድ ረገድ ጥረታቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አሳስበዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0