ሩሲያ ለኢትዮጵያ ተማሪዎች የምትሰጠውን የነፃ ትምህርት እድል ለመጨመር ወሰነች

ሰብስክራይብ
ሩሲያ ለኢትዮጵያ ተማሪዎች የምትሰጠውን የነፃ ትምህርት እድል ለመጨመር ወሰነችይህ የተገለፀው የሩሲያ ሰብዓዊ ኤጀንሲ ሮሶትሩድኒቼስቶቭ ኃላፊ ኢቭጌኒ ፕሪማኮቭ በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።የኤጀንሲው ኃላፊ ኢቭጌኒ ፕሪማኮቭ ሩሲያ በትምህርት፣ በሳይንስ እና በባህል ዘርፎች ዙሪያ በኢትዮጵያ ስለወጠነቻቸው እቅዶች በውይይቱ ወቅት ገልጸዋል። የሩሲያ መንግሥት ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የሚሰጠውን የነፃ ትምህርት ዕድል ለመጨመር እና በአዲስ አበባ የሚገኘውን የሩሲያ የባህል ማዕከል ለማጠናከር መወሰኑንም ተናግርዋል።አምባሳደር ገነት በበኩላቸው ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የሚሰጠው የትምህርት እድል ከፍ እንዲል በመደረጉ ምስጋናቸውን ገልጸዋል ያለው ሞስኮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነው፡፡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0