በታንዛኒያ በኤምፖክስ የተያዙ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሰዎች መገኘታቸውን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

ሰብስክራይብ
በታንዛኒያ በኤምፖክስ የተያዙ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሰዎች መገኘታቸውን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ ሁለቱ ግለሰቦች ሽፍታ፣ ትኩሳት፣ ራስ ምታት እንዲሁም የሰውነት እና የጉሮሮ ህመም እንዳለባቸውና እንዲለዩ መደረጉን የታንዛኒያ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል። በበሽታው ከተያዙት መካከል አንደኛው ከጎረቤት ሀገር ወደ ታንዛኒያ የገባ የከባድ መኪና ሹፌር እንደሆነ ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስታውቋል። መንግሥት በድንበር መግቢያ እና መውጫ ምርመራ በማካሄድ፣ የጤና ግንዛቤን በማሳደግ እና በሕዝባዊ ንቅናቄ ዜጎች መከላከያ እርምጃዎችን እንዲወስዱ በማድረግ በየደረጃው የበሽታ መከላከል ሥራውን አጠናክሮ እንደቀጠለ ሚኒስቴሩ አክሎ ገልጿል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0