እንጆሪ እና ሳፍሮን ያለ አፈር ማምረት የሚያስችል ዘመናዊ አሠራር ለኢትዮጵያ ያስተዋውቃል የተባለ ኩባንያ ወደ ሥራ ሊገባ ነው

ሰብስክራይብ
እንጆሪ እና ሳፍሮን ያለ አፈር ማምረት የሚያስችል ዘመናዊ አሠራር ለኢትዮጵያ ያስተዋውቃል የተባለ ኩባንያ ወደ ሥራ ሊገባ ነውፋብሪካው አፍሪካን ፋርሚንግ ኢንዱስትሪስ፤ በሁለት ሚሊዮን ዶላር ካፒታል እንጆሪ እና ለመድኃኒት ግብዓት የሚውል ሳፍሮን የተሰኘ አበባ በማምረት ለውጪ ገበያ ያቀርባል ተብሏል።ኩባንያው ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው እለት ተፈራርሟል፡፡ የመግባቢያ ስምምነቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ እና የአፍሪካን ፋርሚንግ ኢንዱስትሪስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ናሱር ማሃማት ተፈራርመዋል፡፡አፍሪካን ፋርሚንግ ኢንዱስትሪስ ኩባንያ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ አምስት ሺህ ካሬ ሜትር የለማ መሬት እና ሶስት ሺህ ካሬ ሜትር ሼድ ተረክቦ ወደ ሥራ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡ኩባንያው ሥራ ሲጀምር ያለ አፈር ምርት ማምረት የሚያስችለውን ዘመናዊ አሠራር (hydroponics and vertical farming) ለኢትዮጵያ እንደሚያስተዋውቅ የኢትዮጵያ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በማህበራዊ ትሥሥር ገፁ አስታውቋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0