ታንዛኒያ ከኢትዮጵያ የምታስገባው የኤሌክትሪክ ኃይል ዋጋ ተመጣጣኝ ነው አለች

ሰብስክራይብ
ታንዛኒያ ከኢትዮጵያ የምታስገባው የኤሌክትሪክ ኃይል ዋጋ ተመጣጣኝ ነው አለችየታንዛኒያ መንግሥት ያለበትን የኃይል እጥረት ለመቅረፍ በኬኒያ በኩል ከኢትዮጵያ ሊያስገባ ካሰበው የኤሌክትሪክ ኃይል ጋር ተያይዞ የተነሳወን ስጋት እንደተከላከለ ዘ ሲቲዝን ዘግቧል፡፡ የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሃሳን ውሳኔው ቴክኒካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግምቶችን ግንዛቤ ውስጥ የከተተ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ከታንዛኒያ ደቡብ ምስራቅ ክልል ወደ ሰሜን ዞን የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፍ ከፍተኛ የሆነ የኃይል ብክነት እንደፈጠረ ገልጸው፤ የሀገር ውስጥ አቅርቦት አስተማማኝ አይደለም ብለዋል።ከኢትዮጵያ የሚገባው የኤሌክትሪክ ኃይል ከአንዳንድ የሀገር ውስጥ የኃይል ማመንጫዎች ዋጋ የበለጠ ተመጣጣኝ ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ የታንዛኒያ መንግሥት ቃል አቀባይ ጌርሰን ምሲግዋ በጉዳዩ ዙርያ ባወጡት መግለጫ ተናግረዋል። "ከኢትዮጵያ በኬንያ በኩል የሚገባው የኤሌክትሪክ ኃይል ተደጋጋሚ መቆራረጦችን ለማስወገድ እና በረዥም ርቀት ማስተላለፊያ የሚደርሰውን ከፍተኛ የኃይል ብክነት ለመቀነስ ይረዳል" ሲሉ ቃል አቀባዩ አክለዋል፡፡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0