ኢትዮጵያ ለስድስት ወራት የሚቆይ ፀረ-ብክለት ዘመቻ መጀመሯን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ ለስድስት ወራት በሚቆየው የፀረ-ብክለት ዘመቻ የአረንጓዴ አካባቢ ግንዛቤን በህብረተሰቡ ዘንድ ለማስረጽ አቅዶ እየሰራ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል። ለሁለተኛ ገዜ የሚካሄደው ይህ ዘመቻ "ጽዳትና አረንጓዴን የኢትዮጵያ ባህል ማድረግ" በሚል መሪ ቃል በቅርቡ ይጀመራል ሲሉ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሌሊሴ ነሜ ተናግረዋል።የዘመቻው ዓላማ በአካባቢ ብክለት ዓይነቶች እና ቅድመ መከላከል እርምጃዎች ዙርያ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግና የማህበረሰቡን የተባበረ እርምጃ ወሳኝነት ማጉላት እንደሆነ የባለስልጣኑ ዳይሬክተር ጠቁመዋል። ሌሊሴ አክለውም የፕላስቲክ ብክለት ሕጎችን በትክክል መተግበር፣ ደረቅ እና አደገኛ ቆሻሻዎችን በአግባቡ ማስወገድ እና ሁሉም ፕሮጀክቶቸ የአካባቢ እና የማህበራዊ ተፅእኖ ግምገማን እንዲያከብሩ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተው፤ ይኽንን በሚጥሱት ላይ ሕጋዊ ቅጣት ይጣላል ብለዋል። የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በዘመቻው ላይ በጋራ መሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር ባሳለፍነው ሳምንት ተፈራርሟል፡፡በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ኢትዮጵያ ለስድስት ወራት የሚቆይ ፀረ-ብክለት ዘመቻ መጀመሯን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ
ኢትዮጵያ ለስድስት ወራት የሚቆይ ፀረ-ብክለት ዘመቻ መጀመሯን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ
Sputnik አፍሪካ
ኢትዮጵያ ለስድስት ወራት የሚቆይ ፀረ-ብክለት ዘመቻ መጀመሯን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ ለስድስት ወራት በሚቆየው የፀረ-ብክለት ዘመቻ የአረንጓዴ አካባቢ ግንዛቤን በህብረተሰቡ ዘንድ ለማስረጽ አቅዶ እየሰራ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል።... 10.03.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-03-10T11:54+0300
2025-03-10T11:54+0300
2025-03-10T12:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ኢትዮጵያ ለስድስት ወራት የሚቆይ ፀረ-ብክለት ዘመቻ መጀመሯን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ
11:54 10.03.2025 (የተሻሻለ: 12:14 10.03.2025)
ሰብስክራይብ