የሶሪያ የሰብዓዊ መብቶች ታዛቢ አዲሱ የሀገሪቱ መንግሥት 340 ሰዎችን ገድሏል ሲል ወነጀለመቀመጫውን ብሪታኒያ ያደረገው የሶሪያ የሰብዓዊ መብት ታዛቢ ድርጅት "መከላከያ ሚኒስቴሩ እና አጋር ኃይሎች በዘፈቀደ በፈጸሙት የጦር ወንጀል እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት 340 ሰዎች ተገድለዋል" ያለ ሲሆን፤ ከሟቾቹ መካከልም ሴቶች እና ህጻናት እንደሚገኙበት ጨምሮ ገልጿል። በላታኪያ እና ታርቱስ ግዛቶች የተቀሰቀሰው አለመረጋጋት ሐሙስ እለት የጀመረ ሲሆን፤ የአይን እማኞች የውጭ ሀገር ተዋጊዎች በአካባቢው ገብተዋል ሲሉ ለስፑትኒክ ተናግረዋል። "ከየት እንደመጡ ባላውቅም፤ አረብኛ ግን አያወሩም። ያገኙት ላይ በመተኮስ፤ መሸሽ ያልቻሉትን ይዘዋል። ከቤታችን መውጣት ፈርተናል፤ ምግብ እና ውሃ እያለቀብን ነው” ሲል አንድ የአይን እማኝ ተናግሯል። ሌሎች እማኞች በላታኪያ ጎዳናዎች ያልተቋረጠ የጥይት ተኩስ እና እስር እንደነበር ተናግረዋል። "የታጠቁ ሚሊሻዎች ሱቆችን በመውረር ያገኙትን ይዘርፋሉ። ሃሜሚም በሚገኘው የላታኪያ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ብዙ ሰዎች እንደተሰበሰቡ በኢንተርኔት አይተናል፤ አሁን ግን መሄድ አደገኛ ነው፤ ምክንያቱም ልትታሰር ወይም ልትገደል ትችላለህ" ሲል ሌላኛው እማኝ ገልጿል። የማህበራዊ ትሥሥር ገጽ ምስሎች ግጭቱን የሚሸሹ ሲቪሎች ላታኪያ ወደሚገኘው የሩሲያ ሃሜሚም አየር ማረፊያ ለመሸሸግ ሲሄዱ ያሳያሉ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የሶሪያ የሰብዓዊ መብቶች ታዛቢ አዲሱ የሀገሪቱ መንግሥት 340 ሰዎችን ገድሏል ሲል ወነጀለ
የሶሪያ የሰብዓዊ መብቶች ታዛቢ አዲሱ የሀገሪቱ መንግሥት 340 ሰዎችን ገድሏል ሲል ወነጀለ
Sputnik አፍሪካ
የሶሪያ የሰብዓዊ መብቶች ታዛቢ አዲሱ የሀገሪቱ መንግሥት 340 ሰዎችን ገድሏል ሲል ወነጀለመቀመጫውን ብሪታኒያ ያደረገው የሶሪያ የሰብዓዊ መብት ታዛቢ ድርጅት "መከላከያ ሚኒስቴሩ እና አጋር ኃይሎች በዘፈቀደ በፈጸሙት የጦር ወንጀል እና የሰብዓዊ መብት... 09.03.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-03-09T20:09+0300
2025-03-09T20:09+0300
2025-03-09T21:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የሶሪያ የሰብዓዊ መብቶች ታዛቢ አዲሱ የሀገሪቱ መንግሥት 340 ሰዎችን ገድሏል ሲል ወነጀለ
20:09 09.03.2025 (የተሻሻለ: 21:44 09.03.2025)
ሰብስክራይብ