የዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ባለስልጣናት የአማፂያን መሪዎች ያሉበትን ለጠቆመ የ5 ሚሊዮን ዶላር ጉርሻ አቀረቡ

ሰብስክራይብ
የዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ባለስልጣናት የአማፂያን መሪዎች ያሉበትን ለጠቆመ የ5 ሚሊዮን ዶላር ጉርሻ አቀረቡ "በፍርድ ወንጀለኛ የተባሉትን ኮርኒል ናንጋ፣ በርትራንድ ቢሲሚዋ እና ሱልጣኒ ማኬንጋን እስር የረዳ ማንኛውም ሰው የ5 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ያገኛል። በተጨማሪም የሸሹ ግብረ አበሮቻቸውን ፔሮት ሉዋራ፣ ኢሬንጅ ባሌንጌ እና ሌሎች በፍትሕ የሚፈለጉ ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያስችል መረጃ የሰጠ የ4 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ያገኛል" ሲል የሀገሪቱ ፍትሕ ሚኒስቴር ገልጿል። ናንጋ የኮንጎ ወንዝ ጥምረት (ኤኤፍሲ) በመባል የሚታወቀው አማፂ ቡድን መሪ ነው። ባለፈው ክረምት የኮንጎ ፍርድ ቤት በጦር ወንጀል እና በሀገር ክህደት ወንጀል በሌለበት የሞት ፍርድ ፈርዶበታል። ናንጋ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽን ኃላፊ ሆኖ አገልግሏል። ቢሲምዋ ከኤኤፍሲ ጋር ግኑኝነት ያለውን የኤም23 ቡድን የፖለቲካ ክንፍ የሚመራ ሲሆን ማኬንጋ የኤም23 ጦር አዛዥ ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0