በኮንጎ የደቡብ አፍሪካ ጦር ስምሪት በአፍሪካ ክልላዊ ድርጅቶች ውሳኔ ላይ እንደሚመሠረት የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ተናገሩ

ሰብስክራይብ
በኮንጎ የደቡብ አፍሪካ ጦር ስምሪት በአፍሪካ ክልላዊ ድርጅቶች ውሳኔ ላይ እንደሚመሠረት የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ተናገሩ የደቡብ አፍሪካ መከላከያ ሚኒስትር አንጀሊና ሞትሼክጋ "የግምገማ ሂደት በመካሄድ ላይ ይገኛል" ማለታቸውን ዘገባዎች ያመላከቱ ሲሆን፤ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ (ኢኤሲ) እና የደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ (ሳድክ) የደቡብ አፍሪካ ጦር ስምሪትን አስመልከቶ ዋና ውሳኔ ሰጪዎች መሆናቸውን ገልፀዋል። "ደቡብ አፍሪካ በእነዚህ አካላት አመራር ሰጪነት ትንቀሳቀሳለች፤ የመውጣት ወይሞ የመቆየት ውሳኔው እነዚህ አካላት በሚሰጡት አቅጣጫ እና ውሳኔ ይመሠረታል።" ኢኤሲ እና ሳድክ በምስራቅ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ስላለው ሁኔታ ለመወያየት በዚህ ዓመት ለሁለተኛ ግዜ የመሪዎች ስብሰባ ለማካሄድ ማቀዳቸውንም ጠቅሰዋል።  የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሮናልድ ላሞላ የሳድክ ሰላም አስከባሪ ኃይል አካል የሆነው የሀገሪቱ ጦር ከምስራቅ ኮንጎ በችኮላ እንደማይወጣ ቀደም ሲል ተናግረው ነበር። የደቡብ አፍሪካ ጦር ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አይሸሽም ሲሉም ነበር ጨምረው የገለፁት።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0