የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞስኮ ዕለታዊ በረራዎችን ለማጀመር እንዳቀደ ይፋ አደረገ "የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጪው ጥቅምት ጀምሮ በየቀኑ ወደ ሞስኮ ይበራል ብለን ሙሉ ተስፋ እናደርጋለን" ሲሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ለማ ያዴቻ ለስፑትኒክ አፍሪካ አረጋግጠዋል። ኃላፊው አክለውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኢትዮጵያን ከሩሲያ ከማገናኘት ባለፈ፤ ሩሲያን ከአፍሪካ እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ ገበያዎች ጋር ለማስተሳሰር ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት አጽንኦት ሰጥተዋል። በተጨማሪም አየር መንገዱ የኢትዮጵያን የብሪክስ አባልነት በመጠቀም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ተደራሽነት ለማሳደግ እንደተዘጋጀ ተናግረዋል። "በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ...ኢትዮጵያ ከቻይና እስከ ብራዚል ድረስ በብሪክስ እምብርት ላይ ትገኛለች" ያሉት ኃላፊው "የብሪክስ ቡድን አባል መሆኑ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በሕዝብ ለህዝብ ግንኙነት የጋራ እድል ይዞ ይመጣል" ሲሉም አብራርተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞስኮ ዕለታዊ በረራዎችን ለማጀመር እንዳቀደ ይፋ አደረገ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞስኮ ዕለታዊ በረራዎችን ለማጀመር እንዳቀደ ይፋ አደረገ
Sputnik አፍሪካ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞስኮ ዕለታዊ በረራዎችን ለማጀመር እንዳቀደ ይፋ አደረገ "የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጪው ጥቅምት ጀምሮ በየቀኑ ወደ ሞስኮ ይበራል ብለን ሙሉ ተስፋ እናደርጋለን" ሲሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ዘርፍ ዋና ሥራ... 09.03.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-03-09T10:06+0300
2025-03-09T10:06+0300
2025-03-09T10:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞስኮ ዕለታዊ በረራዎችን ለማጀመር እንዳቀደ ይፋ አደረገ
10:06 09.03.2025 (የተሻሻለ: 10:44 09.03.2025)
ሰብስክራይብ