የህዳሴ ግድብ በቀን በአማካኝ ከ14 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የዓሳ ምርት እያስገኘ ነው ተባለ

ሰብስክራይብ
የህዳሴ ግድብ በቀን በአማካኝ ከ14 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የዓሳ ምርት እያስገኘ ነው ተባለ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2017 በጀት ዓመት ስምንት ወራት 3 ሺህ 700 ቶን ዓሳ የተመረተ ሲሆን፤ 95 በመቶ የሚሆነው የዓሳ ምርት ከዓባይ ግድብ የተገኘ ነው። ይኼም በቀን በአማካኝ 14 ሺህ 646 ኪሎ ግራም የዓሳ ምርት ይገኛል ማለት ነው ሲል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግብርና ቢሮ አስታውቋል። ከዚህ በፊት ይገኝ የነበረው ዓመታዊ የዓሳ ምርት ከ1 ሺህ 200 ቶን ያልበለጠ እንደነበር ተገልጿል። በክልሉ አንድ ኪሎ ግራም ዓሳ 400 ብር እየተሸጠ እንደሆነ የክልሉን የግብርና ቢሮ ኃላፊ ጠቅሶ የመንግሥት ሚዲያ ዘግቧል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0