የጋናው መሪ ማሃማ ለመጀመርያው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ክዋሜ ንክሩማህ ከስልጣን መውረድ ተጠያቂው ሲአይኤ ነው አሉ

ሰብስክራይብ
የጋናው መሪ ማሃማ ለመጀመርያው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ክዋሜ ንክሩማህ ከስልጣን መውረድ ተጠያቂው ሲአይኤ ነው አሉ ጆን ድራማኒ ማሃማ በ68ኛው የጋና የነጻነት ቀን በዓል ዝግጅት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ይፋ የሆኑ የአሜሪካ ሰነዶች ማዕከላዊ የስለላ ኤጀንሲ (ሲአይኤ) ንክሩማህ በውጪ በነበሩበት ወቅት ከስልጣን የተወገዱበትን መፈንቅለ መንግሥት እንዳቀነባበረ አረጋግጠዋል ብለዋል። የታሪክ መዛግብቱ "ግልጽ" ናቸው ሲሉ አስረግጠዋል። ፕሬዝዳንቱ በመቀጠልም ሴራው ጋና ለዓመታት እንዳትረጋጋ እንዳደረገ እና የንኩሩማህን የጋና ራዕይ እንዳመከነ ተናግረዋል። ንክሩማህ እ.አ.አ 1966 ወደ ቻይና እና ሰሜን ቬትናም በተጓዙበት ወቅት የሀገሪቱ ወታደራዊ እና ፖሊስ፤ በሲቪል ሰርቪሱ በመታገዝ ባካሄዱት መፈንቅለ መንግሥት ከስልጣን ተነስተዋል። የሲአይኤ የአንጎላ ግብረ ኃይል የቀድሞ ኃላፊ የነበሩት ጆን ስቶክዌል፤ በአክራ የሲአይኤ ሰላዮች "ከሴረኞቹ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበራቸው" ሲሉ ጽፈዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0