ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ በዓለም ላይ ተፅዕኖ እንድታሳድር እና ቅቡልነቷ እንዲያድግ ያግዛታል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት ተመራማሪ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ በዓለም ላይ ተፅዕኖ እንድታሳድር እና ቅቡልነቷ እንዲያድግ ያግዛታል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት ተመራማሪ ተናገሩ በወጭ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ሃይማኖት እሸቱ፤ የኢትዮጵያ የብሪክስ ተሳትፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገራዊ ጥቅሟን ከማስጠበቅ ባለፈ በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት ለመቆም የሚያስችል መድረክ ፈጥሯል ብለዋል። ኢትዮጵያ በብሪክስ ሕብረት ውስጥ መካተቷ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚደረጉ ውይይቶች በተለይም በእኩልነት፣ በፍትህ እና በልማት ጉዳዮች ላይ ድምጿ እንዲሰማ ይረዳል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።"በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን የጋራ የልማት ጥረት ለማጠናከር እና የደቡብ-ደቡብ ትብብርን ለማጎልበት የብሪክስ አባልነት አስተዋፅኦ ያደርጋል። ከሁሉም በላይ አባልነቱ ለዘላቂ ልማት አማራጭ የፋይናንስ መፍትሄዎችን ለማግኘት በጣም ወሳኝ ሊሆን ይችላል" ሲሉ ተመራማሪው ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0