ደቡብ ሱዳን በእስር ላይ የነበሩትን የሰላም ግንባታ ሚኒስትር ከእስር እንደፈታች ዘገባዎች አመላከቱ

ሰብስክራይብ
ደቡብ ሱዳን በእስር ላይ የነበሩትን የሰላም ግንባታ ሚኒስትር ከእስር እንደፈታች ዘገባዎች አመላከቱ በቅርቡ የተካሄዱትን እስሮች ተከትሎ በሀገሪቱ ውጥረት በመንገሱ፤ ለፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ታማኝ የሆኑ ኃይሎች የተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር ቁልፍ አጋር የሆኑትን የሰላም ግንባታ ሚኒስትር ስቴፈን ፓር ኩዎልን ከእስር እንደፈቱ የማቻር ቃል አቀባይ ፑክ ቦዝ ባሉአንግ ተናግረዋል።ሆኖም ሌሎች የማቻር አጋሮች የነዳጅ ሚኒስትሩ እና የጦር ሰራዊቱ ምክትል አዛዥን ጨምሮ አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ። የጸጥታ ኃይሎች ባለስልጣናቱ የሀገሪቱን የእርስ በርስ ጦርነት ተከትሎ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አደጋ ላይ የሚጠሉ ድርጊቶች ላይ ተሳትፈዋል በማለት በዚህ ሳምንት በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸው ተገልጿል፡፡ውጥረቱ ከማቻር የኑዌር ብሔረሰብ የተውጣጣው የኋይት አርሚ ሚሊሻ ስትራቴጂካዊ ቦታ በሆነችው ናስር ከተማ ከብሔራዊ ኃይሉ ጋር የገባውን ግጭት ተከትሎ የመጣ ነው። የኋይት አርሚ እ.አ.አ. ከ2013 እስከ 2018 በዘለቀው የእርስ በርስ ግጭት ከማቻር ጦር ጋር በመሆን የኪር ዲንቃ ሠራዊትን ተዋግተዋል። መንግሥት ስለ እስሩ ምንም ዓይነት መግለጫ ባይሰጥም፤ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ሚካኤል ማኩዪ፤ የማቻር ኃይሎች ከኋይት አርሚ ጋር በመሆን በናስር አቅራቢያ በሚገኝ ወታደራዊ ጦር ሰፈር ላይ ጥቃት ፈጽመዋል በማለት የወነጀሉ ሲሆን፤ የማቻር ፓርቲ ግን ይህን አስተባብሏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0