ሩሲያ እና አሜሪካ በስትራቴጂካዊ የጦር መሳሪያዎች ዙሪያ ንግግር ሊያደረጉ ይገባል ሲል ክሬምሊን ገለጸ

ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና አሜሪካ በስትራቴጂካዊ የጦር መሳሪያዎች ዙሪያ ንግግር ሊያደረጉ ይገባል ሲል ክሬምሊን ገለጸየሩሲያ ፕሬዝዳንታዊ ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ በዚህ ንግግር ወቅት በተለይም ከማክሮን አስተያየት ጋር በተገናኘ፤ በአውሮፓ ውስጥ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ መኖሩን ችላ ማለት እንደማይቻል በአጽንኦት ተናግረዋል።ዲሚትሪ ፔስኮቭ ያነሷቸው ተጨማሪ ሃሳቦች፡- 🟠 የአውሮፓ ሕብረት ጠብ አጫሪ ንግግሮች በዩክሬን ውስጥ ያለውን ቀውስ ለመፍታት ከሚደረገው ጥረት ጋር ተቃራኒ ናቸው፡፡🟠 አዲስ መረጃ ባይኖርም ሩሲያ እና አሜሪካ በዩክሬን ጉዳይ ለመወያየት ዝግጅት እያደረጉ ነው።🟠 በዩክሬን ጉዳይ ከአሜሪካ ጋር ለሚደረገው ድርድር ሩሲያ ተደራዳሪዋን ገና አልመረጠችም፡፡🟠 ከዩክሬን ጋር ለሚደረጉት ድርድሮች ሩሲያ በኢስታንቡል የተደረሰውን ስምምነት እንደ መነሻ መቁጠሯን ትቀጥላለች፡፡ 🟠 ሩሲያ ለአውሮፓ ሕብረት ወታደራዊ ዝግጅት አፀፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ልትገደድ ትችላለች፡፡ 🟠 የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ቁጥጥርን በተመለከተ ከቤጂንግ ጋር ያለው ጉዳይ እልባት አላገኘም። በዚህ ጉዳይ ዙርያ ቻይና የያዘችው አቋም ግልጽ አይደለም፡፡🟠 ሩሲያ ስትራቴጂክ ደህንነትን በተመለከተ ከቻይና ጋር የምታደርገውን ንግግር አጠናክራ ትቀጥላለች፡፡ 🟠 በጦር መሳሪያ ቁጥጥር ዙሪያ በሚካሄደው ውይይት የአውሮፓ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ክምችት ግምት ውስጥ መግባት አለበት።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0