የኢጋድ ማቋቋሚያ ስምምነት ለሶማሊያ ፓርላማ ቀረበ የሶማሊያ ካቢኔ ለምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የማቋቋሚያ ስምምነት ድጋፍ በመስጠት እንዲፀድቅ ወደ ሀገሪቱ ፓርላማ መርቷል። ኢጋድ ባወጣው መግለጫ ውሳኔው ሶማሊያ ለባለብዙ ወገን ትብብር እንዲሁም ለቀጣናው ሰላም፣ መረጋጋት እና ልማት ቁርጠኛ እንደሆነች የሚያሳይ ነው ብሏል። የተሻሻለው የኢጋድ ስምምነት በአባል ሀገራቱ መካከል ያለውን የትብብር አድማስ በማስፋት የቀጣናውን ፈተናዎች በመቅረፍ በኩል ጠንካራ መሠረት እንደሚጥል ተገልጿል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት መሥራች የሆነችው ሶማሊያ ከጂቡቲ፣ ኢትዮጵያ እና ኬኒያ በመቀጠል ለኢጋድ የመመሥረቻ ስምምነት ቁርጠኝነቷን የገለፀች ሀገር ሆናለች። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የኢጋድ ማቋቋሚያ ስምምነት ለሶማሊያ ፓርላማ ቀረበ
የኢጋድ ማቋቋሚያ ስምምነት ለሶማሊያ ፓርላማ ቀረበ
Sputnik አፍሪካ
የኢጋድ ማቋቋሚያ ስምምነት ለሶማሊያ ፓርላማ ቀረበ የሶማሊያ ካቢኔ ለምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የማቋቋሚያ ስምምነት ድጋፍ በመስጠት እንዲፀድቅ ወደ ሀገሪቱ ፓርላማ መርቷል። ኢጋድ ባወጣው መግለጫ ውሳኔው ሶማሊያ ለባለብዙ ወገን... 07.03.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-03-07T11:16+0300
2025-03-07T11:16+0300
2025-03-07T11:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий