🪖 ኢትዮጵያ ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ ከጥይት ሽያጭ 30 ሚሊየን ዶላር ገቢ እንዳገኘች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለፁ

ሰብስክራይብ
🪖 ኢትዮጵያ ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ ከጥይት ሽያጭ 30 ሚሊየን ዶላር ገቢ እንዳገኘች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለፁጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሆሚቾ የጥይት ማምረቻ ፋብሪካን በትንትናው እለት ጎብኝተዋል። በዚህም ወቅት ኢትዮጵያ ተተኳሽ ከማምረት አልፋ ወደ ውጭ የመላክ አቅሟን እንዳሳደገች ገልፀዋል።ኢትዮጵያ ክላሽ፣ ብሬን፣ ስናይፐር፣ ዲሽቃ፣ ታንክ እና ሁሉንም ዓይነት መድፎች ከሀገር ውስጥ ፍላጎት ባለፈ ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንደቻለችም ተናግረዋል፡፡ ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ ከ30 ሚሊየን ያላነሰ ዶላር የጥይት ሽያጭ እንደተፈፀመም ነው ያስታወቁት፡፡  “ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ ተተኳሽ ጥይቶችን የማምረት ሙከራዎች ቢኖሩም እስከ ዛሬ ሶስት ዓመት ድረስ ከውጭ በማስገባት ላይ ተመሥርታ ቆይታለች። አሁን ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ተተኳሽ የማምረት አልፎም ወደ ውጭ የመላክ አቅም አሳድጋለች” ሲሉ በማህበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ይፋ አድርገዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0