ማክሮን ለራሳቸውም ሆነ ለፈረንሳይ ሚና ለመስጠት እየተፍጨረጨሩ ነው ሲሉ አንድ ተንታኝ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ማክሮን ለራሳቸውም ሆነ ለፈረንሳይ ሚና ለመስጠት እየተፍጨረጨሩ ነው ሲሉ አንድ ተንታኝ ተናገሩ "የማክሮን አመለካከቶች አሁን ካለው የአሜሪካ መንግሥት ጋር ፍጹም ተቃራኒ ናቸው።  ማክሮን እና ስታርመር፤ እወነቱ ሀገሮቻቸው ሁለተኛውን የዓለም ጦርነት እንዳላሸነፉ እና ቀሪው የኒውክሌር አቅማቸው ከጦርነቱ በኋላ አሜሪካ  ባዋቀረችው ማዕቀፍ ውስጥ ብቻ እንዳለ ማስታወስ አለባቸው" ሲሉ ብራሰልስ በሚገኘው የሲፒአይ ፋውንዴሽን የስትራቴጂክ ተንታኝ እና ዳይሬክተር ፓኦሎ ራፎን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።የማክሮን አስተያየት በኧርሰላ ቮን ደር ሌይን ዳግም የመታጠቅ እቅድ ጥርጣሬ ውስጥ የወደቀውን የአውሮፓ ሕብረት ምክር ቤት ይበልጥ ይከፋፍለዋል የሚል ዕምነት እንዳላቸው አክለዋል።"እንደ ጣሊያን፣ ጀርመን፣ ፖላንድ እና ግሪክ ያሉ ሀገራት የደህንነት እና የመከላከያ መርሆችን እና ፍላጎቶችን ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ እየቀላቀሉ የሚገኙትን ማክሮን፣ ስታርመር እና ኧርሰላ ቮን ደር ሌይንን በግልጽ ውድቅ እንደሚያደርጉ መገመት ይቻላል" ሲሉ ራፎን ተናግረዋል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0