ታማኙ የሰቆጣ ባጃጅ አሽከርካሪ ተሳፋሪ ረስቶ የወረደውን 82 ሺህ 265 ብር መለሰ

ሰብስክራይብ
ታማኙ የሰቆጣ ባጃጅ አሽከርካሪ ተሳፋሪ ረስቶ የወረደውን 82 ሺህ 265 ብር መለሰበአማራ ክልል ሰቆጣ ከተማ በባጃጅ አሽከርካሪነት የሚሠራው ወጣት ሰለሞን ቢምረው፤ ከተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር ለባለቤቱ መልሷል፡፡ ብሩን ባጃጅ ውስጥ የረሱት ሴት ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው ገንዘቡን ሲፈልጉ እንደነበር ነው የተነገረው፡፡ አሽከርካሪውም በፊናው ተሳፋሪዋን ሲፈልግ ቆይቶ በመጨረሻም እንደተገናኙና በፖሊስ ፊት ንብረቱን እንደተረካከቡ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ፤ አሽከርካሪው ከአሁን ቀደምም ባጃጁ ውስጥ የተጣለ ሞባይል አግኝቶ ለተሳፋሪ በታማኝነት መመለሱን አስታውሷል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0