‍ዝነኛው የእግር ኳስ ተጫዋች ቤኒ ማካርቲ የኬንያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ

ሰብስክራይብ
‍ዝነኛው የእግር ኳስ ተጫዋች ቤኒ ማካርቲ የኬንያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመየቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ የአጥቂዎች አሰልጣኝ ቤኒ ማካርቲ የኬንያ የወንዶች ብሔራዊ ቡድን ሃራምቤ ስታርስ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ተሹሟል። “እዚህ በመሆኔ ደስተኛ ነኝ። ብዙ አቅም ያለው የብሔራዊ ቡድን የማሰልጠን ኃላፊነትን በመውሰዴ ኩራት ይሰማኛል" ሲል አዲሱ የኬንያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ተናግሯል። ማካርቲ በመጪው ነሐሴ ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ታንዛኒያ በጥምረት በሚያዘጋጁት የቶታል ኢነርጂ የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ እንዳቀደ አስታውቋል። ኬኒያ በ2026 ለሚካሄደው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ለማለፍ ጋምቢያን ከሜዳዋ ውጭ፤ ጋቦንን ደግሞ በሜዳዋ በመጋቢት ወር ታስተናግዳለች። በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0