ኢትዮጵያ በቻርጅ የሚሠራ ስኩተር ማምረት ጀመረች

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በቻርጅ የሚሠራ ስኩተር ማምረት ጀመረችኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ ቢሾፍቱ በሚገኘው አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ውስጥ በቻርጅ የሚሠራ ስኩተር ማምረት መጀመሩን በትላንትናው እለት አስታውቋል፡፡ስኩተሮቹ በአንድ ቻርጅ እስከ 30 ኪ.ሜ የሚጓዙ፣ የፓርኪንግ ቦታ የማይፈልጉ እና ክብደታቸው 15 ኪ.ግ ብቻ በመሆኑ በቀላሉ ወደ ቢሮና ቤት ለመግባት የሚችሉ ናቸው ተብሏል።ከአከባቢ ብክለት ነጻ ናቸው የተባሉት ስኩተሮቹ፤ የትራንስፖርት ችግር የሚያቃልሉ እና ዘመናዊ ትራንስፖርትን የሚያሳልጡ እንደሆነም ነው የተነገረው፡፡የኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ቡድን ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ፤ ስኩተሮቹ እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ላይ አማራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጡና በቅርብ ቀን ወደ ገበያ እንደሚወጡ ገልፀዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0