የአዲስ አበባን ቱሪዝም የማሳደግ ዓላማ ያለው የእግረ መንገድ ቱሪዝም "የስቶፕ ኦቨር ቱሪዝም" የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ

ሰብስክራይብ
የአዲስ አበባን ቱሪዝም የማሳደግ ዓላማ ያለው የእግረ መንገድ ቱሪዝም "የስቶፕ ኦቨር ቱሪዝም" የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመየመግባቢያ ሰነዱን የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትላንትናው እለት ተፈራርመዋል።ስምምነቱ የቱሪስቶችን ቆይታ ለማረዘም በሚያስችለው "ስቶፕ ኦቨር ቱሪዝም" ዘርፍ የተደረገ ሲሆን፤ ተጓዦች በኢትዮጵያ ሲያልፉ ጥቂት ቀናት ቆይታ አድርገው ወደ መዳረሻ ሀገራቸው እንዲሄዱ የሚያስችል የቱሪዝም ዓይነት እንደሆነ ተገልጿል፡፡ስምምነቱ በተጨማሪም የኢትዮጵያን የቱሪዝም ዕድገት ለማፋጠን ያለመና በአዲስ አበባና ልዩ ልዩ ስፍራዎች የቆይታ ግዜ ለሚኖራቸው መንገደኞች በተዘጋጀ ስቶፕ ኦቨር ፓኬጅ ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡ሶስቱ ተቋማት የእግረ መንገድ ቱሪዝምን ለማልማት በተቋማት መካከል ጠንካራ ትሥሥር መፍጠርና የተቀናጀ ጥረት ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ ስምምነቱን በተፈራረሙብት ወቅት ገልጸዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0