ኢትዮጵያ በጂኤምኦ የበቀለ በቆሎ ለንግድ እንዲቀርብ ፈቀደች

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በጂኤምኦ የበቀለ በቆሎ ለንግድ እንዲቀርብ ፈቀደች ብሔራዊ የዝርያ አጽዳቂ ኮሚቴ ባሳለፍነው ሳምንት ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት ኢትዮጵያ በዘረመል ምህንድስና የተለወጠ (ጂኤምኦ) በቆሎ ለገበያ ማቅረብ ትጀምራለች። በዘረመል ምህንድስና የተለወጠው በቆሎ ነፍሳት እና ድርቅ መቋቋም እንደሚችል ተገልጿል።የማፀደቅ ሂደቱ ሰባት ዓመታትን እንደፈጀ እና በሰው፣ እንሰሳት እና አካባቢ ላይ ሊያደርስ የሚችለው ተፅእኖ ተገምግሞ ደህንነቱ እንደተረጋገጠ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል። መንግሥት ከበቆሎ በተጨማሪ የዘረመል ለውጥ ያደረጉ የጥጥ ዝርያዎችም ለገበያ እንዲቀርቡ ፍቃድ ሰጥቷል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0