ሞሪሸስ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለቻጎስ ደሴቶች ስምምነት የሰጡትን ድጋፍ በደስታ እቀበላለሁ አለች

ሰብስክራይብ
ሞሪሸስ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለቻጎስ ደሴቶች ስምምነት የሰጡትን ድጋፍ በደስታ እቀበላለሁ አለች በስምምነቱ መሠረት እንግሊዝ ደሴቶቹ ላይ ታራምድ የነበረውን ሉአላዊነት ለሞሪሸስ በመመለስ፤ የዲያጎ ጋርሺያን የጦር ሰፈር በ99 ዓመት የሊዝ ውል ትቆጣጠራለች። ስምምነቱ በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ድጋፍ ያገኘ ቢሆንም፤ የትራምፕ ዳግም መመረጥ እና በሞሪሸስ ምርጫ ናቪን ራምጎልም ወደ ስልጠን መምጣታቸው እጣ ፈንታውን አጠራጣሪ አድርጎት ቆይቷል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር ጋር በኋይት ኃውስ ባደረጉት ውይይት ስምምነቱን ለመደገፍ ዝግጁ እንደሆኑ ጠቁመዋል። ራምጎላም ከሳምንታዊው የሞሪሸስ ኤል ሄብዶ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ የትራምፕን አስተያየት “አዎንታዊ” ሲሉ የገለፁ ሲሆን፤ የስምምነቱን መጨረሻ መጠበቅ አስፈላጊ እንደሆነ አፅንዖት ሰጥተዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በበኩላቸዉ ከስታርመር ጋር ስለስምምነቱ እንደሚወያዩና “በጣም ጥሩ ውጤት ያስገኛል” ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ለጋዜጠኞች ተናግዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0