የሩሲያ ባህል እና ሳይንስ ማዕከል 129ኛውን የዓደዋ ድል በዓል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፈ

ሰብስክራይብ
የሩሲያ ባህል እና ሳይንስ ማዕከል 129ኛውን የዓደዋ ድል በዓል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፈማዕከሉ ዓድዋ የጀግንነት፣ የአንድነት እና የብሔራዊ ነፃነት ተምሳሌት ነው ሲል ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቱን አስተላልፏል። የዓድዋ ድል በዝግጅትም ሆነ በመሳሪያ የተሻሉ የነበሩትን ቅኝ ገዢዎች ያንበረከከ፤ ለዓለም ተምሳሌት የሆነ ታሪካዊ በዓል እንደሆነ ገልጿል።ሩሲያ የነፃነት እና የሉዓላዊነት እሳቤዎችን በመጋራት፤ ለኢትዮጵያ ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ማድረጓንም አስታውሷል። የሩሲያ በጎ ፍቃደኞች እና የጦር መሳሪያዎች የኢትዮጵያን ጦር በማጠናከር ረገድ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ጠቅሷል። ከዓድዋ ድል በኋላም የሩሲያ ዶክተሮች ለቆሰሉት የህክምና አገልግሎት መስጠታቸውን ማዕከሉ በመግለጫው አንስቷል።ማዕከሉ በመግለጫው የሩሲያ እና ኢትዮጵያ የቆየ እና ጠንካራ ግንኙነት መነሻ የዓድዋ ድል ነው ብሏል።የአፍሪካ አዳዲስ ተራማጅ ትውልዶች ኒዩኮሎኒያሊዝምን እንዲታገሉ፣ የእኩልነት እና የነፃነት እሳቤዎች እንዲስፋፉ ያነሳሳውን ቀን ማዕከሉ በአክብሮት እና በአድናቆት ያስታውሳል ሲል በመግለጫው አመልክቷል።   መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0