ኢትዮጵያ የኬንያን ላሙ ወደብ ተጠቅማ ምርቶችን ለማስገባት እንደተስማማች ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አረጋገጡ

ሰብስክራይብ
 ኢትዮጵያ የኬንያን ላሙ ወደብ ተጠቅማ ምርቶችን ለማስገባት እንደተስማማች ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አረጋገጡ የላሙ ወደብ ከኢትዮጵያ እና ሌሎች የጎረቤት ሀገራት ጋር የተደረገውን ስምምነት ተከትሎ የቀጣናው የንግድ ማዕከል ለመሆን እንደተዘጋጀ የኬንያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። "ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የላሙን ወደብ መጠቀም ለመጀመር ተስማምተናል፤ ይህም ተጨማሪ የስራ እድሎችን ለመፍጠር እና የቀጣናውን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ይረዳል" ሲሉ ፕሬዝዳንት ሩቶ ተናግረዋል። የላሙ ወደብ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ዘመናዊ ማቆሚያዎች ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውንም ፕሬዝዳንቱ ጨምረው ገልጸዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0