🪖 የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለክፍለ ዘመናት ለቆየው ዓለም አቀፋዊ ግጭት አውሮፓን ተወቃሽ አደረጉ

ሰብስክራይብ
🪖 የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለክፍለ ዘመናት ለቆየው ዓለም አቀፋዊ ግጭት አውሮፓን ተወቃሽ አደረጉ የሩሲያው ከፍተኛ ዲፕሎማት በዓለም ላይ የተከሰቱ አብዛኞቹ ጥፋቶች መነሻቸው አውሮፓ አልያም የአውሮፓውያን ፖሊሲ ውጤት ናቸው ብለዋል። በማሳያነትም ቅኝ አገዛዝ፣ የመስቀል ጦርነት፣ የክራይሚያ ጦርነት፣ የናፖሊዮን ወረራ፣ የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት እና አዶልፍ ሂትለርን ጠቅሰዋል። "ታሪክን ወደ ኋላ መለስ ብለን ከተመለከትን አሜሪካኖች የቀስቃሽ ወይም "የማቀጣጠል" ሚና አልተጫወቱም። ከጆ ባይደን የስልጣን ዘመን በኋላ በምክንያት የሚመሩ ግለሰቦች [ስልጣን] ጨብጠዋል። ሁሉንም ጦርነቶች ማቆም እንደሚፈልጉ፤ ሰላም እንደሚፈልጉ በግልጽ ተናግረዋል። የጦርነት ትዕይንቱ እንዲቀጥል የሚፈልገው ማነው? አውሮፓ” ሲሉ ከክራስናያ ዝቬዝዳ ጋዜጣ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ሰርጌ ላቭሮቭ አስረድተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0