ኤለን መስክ ዩናይትድ ስቴትስ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና ከኔቶ መውጣቷን እንደሚደግፍ ገለጸ

ሰብስክራይብ
ኤለን መስክ ዩናይትድ ስቴትስ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና ከኔቶ መውጣቷን እንደሚደግፍ ገለጸ የአሜሪካ ሴኔት ሪፐብሊካኖች ሀገሪቱን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሙሉ በሙሉ ለማስወጣት የሚያስችል ረቂቅ ሕግ በየካቲት ወር አቅርበዋል። ሰነዱ ዩናይትድ ስቴትስ ለተባበሩት መንግሥታት የምትሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ እንድታቋርጥና በድርጅቱ የሰላም ማስከበር ተልእኮዎች የምታደርገውን ተሳትፎ እንድታቆም ይጠይቃል። ጥር 12 ስልጣን የተረከቡት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ብዙም ሳይቆዩ ነበር ፍትሐዊ ነው ያሉትን የፈንድ ፖሊሲ በመጥቀስ ዩናይትድ ስቴትስ ከዓለም የጤና ድርጅት እንድትወጣ የሥራ አስፈፃሚ ትዕዛዝ የፈረሙት። ፕሬዝዳንት ትራምፕ አውሮፓ ለኔቶ የመከላከያ አቅም የምታበረክተው አስተዋፅኦ በቂ አይደለም በማለት ደጋግመው ነቀፋ የሚሠነዝሩ ሲሆን፤ ሁሉም አባል ሀገራት ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት 5 በመቶውን ለመከላከያ ወጪ እንዲያውሉ መጠየቃቸው ይታወሳል። አሜሪካዊው ስራ ፈጣሪ እና ፖድካስተር ፓትሪክ ቤት-ዴቪድ፤ ትራምፕ አውሮፓውያን የኔቶ አጋሮችን ችላ የሚሉት "በኔቶ ሥራ ደስተኛ ስላልሆኑ" ነው ሲል ለአርአይኤ ኖቮስቲ የካቲት ወር ላይ በሰጠው አስተያየት ጠቁሟል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0