129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በሩሲያ ዩኒቨርስቲ ተከበረ በዓሉ “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ ቃል ሞስኮ በሚገኘው ሩድን የወዳጅነት ዩኒቨርስቲ (RUDN Friendship University) ተከብሯል፡፡ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ባዘጋጁት ሥነ-ሥርዓት ላይ ኢትዮጵያዊያን፣ የዩኒቨርስቲው ተወካዮች፣ የተለያዩ ሀገራት ተማሪዎች እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተው እንደነበር በሞስኮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል። የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ በፕሮግራሙ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የዓድዋ ድል የኢትዮጵያን ነፃነትና ሉዓላዊ አንድነት ከማስከበር ባለፈ፤ የፀረ-ቅኝ አገዛዝ ትግሎች በአፍሪካ እና ከአፍሪካ ውጭ በሚገኙ ሀገራት እንዲቀጣጠል በማድረግ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ታሪካዊ የጥቁር ሕዝቦች ድል መሆኑን ገልፀዋል። በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራዎችን፣ ባህላዊ ቁሳቁሶችን እና የቡና አፈላል ስርዓትን በማስተዋወቅ፤ በዓሉ በደማቅ ሁኔታ እንደተከበረ ኤምባሲው በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባጋራው መረጃ አመላክቷል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በሩሲያ ዩኒቨርስቲ ተከበረ
129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በሩሲያ ዩኒቨርስቲ ተከበረ
Sputnik አፍሪካ
129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በሩሲያ ዩኒቨርስቲ ተከበረ በዓሉ “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ ቃል ሞስኮ በሚገኘው ሩድን የወዳጅነት ዩኒቨርስቲ (RUDN Friendship University) ተከብሯል፡፡ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ባዘጋጁት... 01.03.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-03-01T21:08+0300
2025-03-01T21:08+0300
2025-03-01T21:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий