ሩሲያ ለኢትዮጵያ ተማሪዎች የምትሰጠውን የነጻ ትምህርት እድል አጠናክራ እንደምትቀጥል ተገለፀ

ሰብስክራይብ
ሩሲያ ለኢትዮጵያ ተማሪዎች የምትሰጠውን የነጻ ትምህርት እድል አጠናክራ እንደምትቀጥል ተገለፀ ይህ የተገለፀው በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ ከሩሲያ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ምክትል ሚኒስትር ሞጊሌቭስኪ ኮንስታንቲን ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው። የሩሲያው ባለስልጣን የሁለቱ ሀገራት የትምህርት ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና እና ሩሲያ ለኢትዮጵያ ተማሪዎች የምትሰጠውን ነጻ የትምህርት እድል እየጨመረች እንደምትመጣ በውይይቱ ላይ አስታውቀዋል። ሚኒስትሩ የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ቫለንቲና ማትቪዬንኮ በቅርቡ በኢትዮጵያ ባደረጉት የሥራ ጉብኝት፤ የሁለቱን ሀገራት የትምህርት ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት መንገድ ዙርያ ከኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ጋር መምከራቸውን ገልጸዋል።አምባሳደር ገነት ሩሲያ ለኢትዮጵያ ተማሪዎች ለምትሰጠው የትምህርት እድል ምስጋና አቅርበው፤ ሀገራቱ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ጉዳዮች ትብብራቸው እያደገ መምጣቱን ጠቁመዋል ሲል በሞስኮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0