ሩሲያ በተፈጥሮ አደጋዎች መጨመር ምክንያት ወደ አፍሪካ ሀገራት የምትልከው የእህል ምርት ከፍ ሊል ይችላል ሲል በሩሲያ የፋኦ ቢሮ ገለፀ ተደጋጋሚ አሉታዊ የአየር ሁኔታዎች በተለይም የሰሜን እና ምዕራብ አፍሪካ ድርቅ እንዲሁም የሳህል ቀጣና የጎርፍ አደጋ፤ የእህል ፍላጎት እንዲጨምር በማድረጉ ለሩሲያ የኤክስፖርት እድል ፈጥሯል ሲሉ በተመድ የምግብ እና ግብርና ድርጅት የሩሲያ አገናኝ ቢሮ አማካሪ ኢጎር ሽፓኮቭ ተናግረዋል። "አፍሪካ ትልቅ የኤክስፖርት መዳረሻ እየሆነች በመምጣቷ፤ ሩሲያ የዚህን ገበያ ፍላጎት የማሟላት እድል አሁንም አላት። እነዚህም ስንዴ በማስገባት ቀዳሚ ሆነው ከቆዩ ሀገራት መካከል ግብፅ፣ አልጄሪያ፣ ሞሮኮ እና ናይጄሪያን ያካትታል። በተጨማሪም አዳዲስ ገበያዎች አሉ። ለምሳሌ ኬንያ ባለፈው ዓመት ከሩሲያ ያስገባችው ስንዴ 40 በመቶ ጨምሯል" ሲሉ የሩሲያው ባለስልጣን ተናግረዋል። በአማካይ 1.6 በመቶ ከሆነው ዓመታዊ ዓለም አቀፍ የሕዝብ እድገት ጋር ሲነፃፀር 2.3 በመቶ የሆነው የአፍሪካ ሕዝብ እድገት፤ አብሮ ከሚጨምረው የእህል ፍጆታ ጋር ተዳምሮ ለዘላቂ ፍላጎት ምክንያት እንደሆነም ጨምረው ገልፀዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ሩሲያ በተፈጥሮ አደጋዎች መጨመር ምክንያት ወደ አፍሪካ ሀገራት የምትልከው የእህል ምርት ከፍ ሊል ይችላል ሲል በሩሲያ የፋኦ ቢሮ ገለፀ
ሩሲያ በተፈጥሮ አደጋዎች መጨመር ምክንያት ወደ አፍሪካ ሀገራት የምትልከው የእህል ምርት ከፍ ሊል ይችላል ሲል በሩሲያ የፋኦ ቢሮ ገለፀ
Sputnik አፍሪካ
ሩሲያ በተፈጥሮ አደጋዎች መጨመር ምክንያት ወደ አፍሪካ ሀገራት የምትልከው የእህል ምርት ከፍ ሊል ይችላል ሲል በሩሲያ የፋኦ ቢሮ ገለፀ ተደጋጋሚ አሉታዊ የአየር ሁኔታዎች በተለይም የሰሜን እና ምዕራብ አፍሪካ ድርቅ እንዲሁም የሳህል ቀጣና የጎርፍ... 01.03.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-03-01T13:06+0300
2025-03-01T13:06+0300
2025-03-01T13:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ሩሲያ በተፈጥሮ አደጋዎች መጨመር ምክንያት ወደ አፍሪካ ሀገራት የምትልከው የእህል ምርት ከፍ ሊል ይችላል ሲል በሩሲያ የፋኦ ቢሮ ገለፀ
13:06 01.03.2025 (የተሻሻለ: 13:44 01.03.2025)
ሰብስክራይብ