ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ በወደብ አጠቃቀም ዙርያ በመጪው ክረምት ስምምነት ይፈራረማሉ ስትል ሶማሊያ አስታወቀች የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አሊ መሐመድ ኦማር ለዩኒቨርሳል ሶማሌ ቲቪ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ በህንድ ውቅያኖስ በኩል ወደብ እንድትጠቀም የሚያስችለው የስምምነት ማዕቀፍ በሰኔ ወር ወይም ከዚያ በፊት ሊፈረም ይችላል። "ማዕቀፉ የወደቡን ዓይነት፣ ትክክለኛ ቦታ እና አጠቃላይ ወጪውን ይወስናል" ሲሉም ባለስልጣኑ ተናግረዋል። የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር የሚደረገው ጥረት በተለይ በፖለቲካዊ ዲፕሎማሲ ማዕቀፍ በተሠሩ ሥራዎች ውጤት መመዝገቡን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነብያት ጌታቸው አርብ እለት ተናግረዋል። ቃል አቀባዩ አክለውም በሀገራቱ መካከል እየታየ ያለው አዲስ የግንኙነት አቅጣጫ፤ ለኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት ብቻ ሳይሆን ለቀጣናው ሰላምና ደህንነት ጭምር ጠቃሚ ነው ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ በወደብ አጠቃቀም ዙርያ በመጪው ክረምት ስምምነት ይፈራረማሉ ስትል ሶማሊያ አስታወቀች
ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ በወደብ አጠቃቀም ዙርያ በመጪው ክረምት ስምምነት ይፈራረማሉ ስትል ሶማሊያ አስታወቀች
Sputnik አፍሪካ
ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ በወደብ አጠቃቀም ዙርያ በመጪው ክረምት ስምምነት ይፈራረማሉ ስትል ሶማሊያ አስታወቀች የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ... 01.03.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-03-01T11:48+0300
2025-03-01T11:48+0300
2025-03-01T12:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ በወደብ አጠቃቀም ዙርያ በመጪው ክረምት ስምምነት ይፈራረማሉ ስትል ሶማሊያ አስታወቀች
11:48 01.03.2025 (የተሻሻለ: 12:14 01.03.2025)
ሰብስክራይብ