የኢትዮጵያ አየር መንገድ በካርጎ አገልግሎት ዘርፍ ሁለት ሽልማቶችን አሸነፈ 

ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በካርጎ አገልግሎት ዘርፍ ሁለት ሽልማቶችን አሸነፈ  የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት የህክምና ቁሳቁሶችን በማጓጓዝ እና አጠቃላይ በካርጎ አገልግሎት ዘርፍ ከአፍሪካ ቀዳሚ በመሆን። የአፍሪካ ምርጥ የፋርማ እቃ ጭነት አገልግሎት አየር መንገድ እና የአፍሪካ ምርጥ የዕቃ ጭነት አገልግሎት አየር መንገድ በመባል ሁለት የአቪየሺን ስኬት ሽልማቶችን አግኝቷል።"ሽልማቶቹ አየር መንገዱ ለልህቀት፣ ፈጠራ እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለደንበኞች ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያመላክቱ ናቸው" ያለው አየር መንገዱ፤ "የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት መዳረሻዎቹንና አገልግሎቶቹን በማስፋፋት የመሪነት ሚናውን ይበልጥ አጠናክሮ ይቀጥላል" ሲል በማኀበራዊ የትስስር ገፁ አስታውቋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0