አዘርባጃን እና ሶማሊያ በነዳጅ እና ጋዝ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሙ

ሰብስክራይብ
አዘርባጃን እና ሶማሊያ በነዳጅ እና ጋዝ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሙ"ሁለቱ ወገኖች የሶማሊያ ተማሪዎች በአዘርባጃን በነዳጅ ዘርፍ ላይ ባተኮሩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሚማሩበት መንገድ ላይ ሀሳብ  ተለዋውጠዋል። በመጨረሻም ‘በአዘርባጃን ሪፐብሊክ የኢነርጂ ሚኒስቴር እና በሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ የነዳጅ እና ማዕድን ሀብት ሚኒስቴር መካከል በተፈጥሮ ጋዝ ዘርፍ የትብብር የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል" ሲል የአዘርባጃን ኢነርጂ ሚኒስቴር ለስፑትኒክ ገልጿል። የሶማሊያ የነዳጅ ሚኒስትር ዳሂር ሽሬ መሐመድ ሰነዱ በተፈረመበት የአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ ከአዘርባጃን ኢነርጂ ሚኒስትር ፓርቪዝ ሻባዞቭ ጋር መነጋገራቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል። ሰነዱ የልምድ ልውውጥን፣ በሁለቱ ሀገራት በሚደረጉ ልዩ ዝግጅቶች ላይ መሳተፍን እንዲሁም በነዳጅ እና ጋዝ ዘርፍ ትብብርን ለማዳበር የጋራ ሴሚናሮች እና መድረኮችን ማዘጋጀትን እንደሚያካትትም ተጠቁሟል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0