የእስራል መከላከያ ጦር የጥቅምት 7ቱን ጥቃት የምርመራ ግኘት ይፋ አደረገ ግኝቱ ከፍተኛ የደህንነት ድክመት እንደነበር አሳይቷል። የታየው ድንገተኛ የአሰራራ ውድቀት ከ1973ቱ የዮም ኪፑር ጦርነት የበለጠ እንደነበር ያትታል። በፈረንጆቹ 2022 ወይም በ2023 በአይሁዶች ፋሲካ (ፓስኦቨር) በዓል ላይ ጥቃት ለመፈፀም ሃማስ ከ2016 ጀምሮ ስልታዊ በሆነ መንገድ እየተዘጋጀ እንደነበር ምርመራው ገልጿል። ሆኖም ለልዩ የኮምንዶ ኃይሎቹ ኑክባዎች ጊዜ ለመስጠት የጥቃቱን ጊዜ አራዝሞታል። ሃማስ በሀምሌ 2023፤ ሄዝቦላህ እና ኢራንን በማስተባበር አጠቃላይ የጦርነት እቅዱን አጠናቋል። ሆኖም ሄዝቦላ በተፈጠረ አለመግባባት ጥቃቱን ለመቀላቀል ማቅማማቱ ነው የተገለፀው። ሪፖርቱ በጥፋተኝነት የፈረጀው ግለሰብ የሌለ ሲሆን የትኛውንም ዓይነት የሥነ-ምግባር ቅጣት ለቀጣዩ የእስራኤል መከላከያ ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ኢያል ዛሚር ትቷል። ተሰናባቹ የእስራኤል መከላከያ ኃይል ዋና አዛዥ ኸርዚ ሃሌቪ በሰጡት የተናጠል መግለጫ፤ በጥቅምት 7ቱ ጥቃት ጦሩን በዋና አዛዥነት በመምራታቸው ለተፈጠረው ስህተት ሙሉ ሃላፊነቱን እወስዳለሁ ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የእስራል መከላከያ ጦር የጥቅምት 7ቱን ጥቃት የምርመራ ግኘት ይፋ አደረገ
የእስራል መከላከያ ጦር የጥቅምት 7ቱን ጥቃት የምርመራ ግኘት ይፋ አደረገ
Sputnik አፍሪካ
የእስራል መከላከያ ጦር የጥቅምት 7ቱን ጥቃት የምርመራ ግኘት ይፋ አደረገ ግኝቱ ከፍተኛ የደህንነት ድክመት እንደነበር አሳይቷል። የታየው ድንገተኛ የአሰራራ ውድቀት ከ1973ቱ የዮም ኪፑር ጦርነት የበለጠ እንደነበር ያትታል። በፈረንጆቹ 2022 ወይም... 28.02.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-02-28T16:01+0300
2025-02-28T16:01+0300
2025-02-28T16:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий