ኒካራጓ ከተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት አባልነቷ እንደምትወጣ የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳት ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ኒካራጓ ከተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት አባልነቷ እንደምትወጣ የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳት ተናገሩ "እነዚህ ተቀባይነት የሌላቸው መዋቅሮች ለኒካራጓ መሠረታቸውን እና ፍሬ ነገራቸውን የሳቱ ናቸው። ለነሱ እውቅና አንሰጥም፤ በሉዓላዊነት፣ በሀገራት እኩልነት ወይም በሕዝቦች ክብር ላይ በሚፈፀም ጥቃት ተሳታፊ ወይም ተባባሪ አንሆንም። በዚህም ኒካራጓ በሉዓላዊ እና የማይሻር ውሳኔዋ ከሰብዓዊ መብት ምክር ቤት እና ከምክር ቤቱ ጋር ተያያዥነት ካላቸው ሁሉም ተግባራት ለመውጣት እንዳሰበች ለመግለፅ ትወዳለች" ሲሉ ምክትል ፕሬዛዳንቷ ሮዛሪዮ ሙሪሎ ተናግረዋል። የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት የባለሙያዎች ቡድን በቅርቡ በኒካራጓ ላይ ያቀረበው ሪፖርት ተቋሙ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን ሲመለከት ከአድልዎ ነፃ፣ ገለልተኛ እና ያለ ልዩነት መሆን አለበት የሚለውን መርህ ጥሷል ሲሉ ለምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ጀርግ ላውበር አስገንዝበዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0