የሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ፀሐፊ ሰርጌ ሾይጉ ቤጂንግ ገቡ

ሰብስክራይብ
የሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ፀሐፊ ሰርጌ ሾይጉ ቤጂንግ ገቡ "የካቲት 17 ፕሬዝዳንት ፑቲን ከቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር ያደረጉትን የስልክ ውይይት ተከትሎ ከሩሲያው መሪ በደረሰኝ ትዕዛዝ መሰረት በእንግዳ ተቀባይዋ ቻይና ገብቻለው። በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ውይይት ለማድረግ መስማማቱ  የሁለትዮሽ ምክክራችንን ልዩ ባህሪ የሚያሳይ ነው" ሲሉ ሾይጉ ከቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ተናግረዋል። ከዚህም በላይ ሩሲያ እና ቻይና ወሳኝ በሆኑ ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ  ተመሳሳይ አቀራረብ እንዳላቸው የገለፁት ባለስልጣኑ፤ ሀገራቱ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በፀጥታው ምክር ቤት፣ በቡድን20፣ በእስያ-ፓሲፊክ የኢኮኖሚ ትብብር እና በሌሎች መዋቅሮች ውስጥ ተመሳሳይ አቋሞችን እንደያዙ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0