ልማት የብሪክስ ተሳትፎ ትኩረት ሊሆን እንደሚገባው የኢትዮጵያ የብሪክስ ተወካይ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ልማት የብሪክስ ተሳትፎ ትኩረት ሊሆን እንደሚገባው የኢትዮጵያ የብሪክስ ተወካይ ተናገሩ የብሔራዊ ባንክ ገዥና የኢትዮጵያ የብሪክስ ተቀዳሚ ተወካይ ማሞ ምህረቱ፤ ኢትዮጵያ ለባለብዙ ወገን ግኑኝነት፣ ለጋራ ደህንነት እና ለዘላቂ ልማት ቁርጠኛ እንደሆነች በብራዚል ተካሂዶ በነበረው የብሪክስ ተወካዮች (ሼርፓስ) ስብሰባ ላይ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ልማት የብሪክስ ተሳትፎ ትኩረት ሊሆን ይገባዋል ብላ እንደምታምን እና ተሳትፎው ተገማች የገበያ አመራጭ በሚፈጥር፣ የልማት ፋይናንስ አሰባሰብን በሚያሳድግ፣ የመሠረተ ልማት ክፍተትን በሚቀርፍ እና ተመራጭ ኢንቨስትመንቶችን በሚስብ መልኩ መሆን እንዳለበት በተወካይዋ በኩል ገልፃለች። ማሞ ምህረቱ አክለውም ኢትዮጵያ የብሪክስ ቤተሰብን ለማጠናከር ቁርጠኛ እንደሆነችና ብሪክስ የበለጠ አካታች እና ወካይ እንዲሆን እንደምትደግፍ ተናግረዋል። ለሁለት ቀናት የተካሄደው የብሪክስ ሼርፓስ ስብሰባ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ከመከረ በኋላ መጠናቀቁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0