ደቡብ አፍሪካ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በብዙ ጉዳዮች ላይ “ትርጉም ያለው ስምምነት” ለማድረግ እንደምትሻ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ደቡብ አፍሪካ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በብዙ ጉዳዮች ላይ “ትርጉም ያለው ስምምነት” ለማድረግ እንደምትሻ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ተናገሩ "እያገኛናቸው ያሉ ምልክቶች የስምምነት ሂደቶችን መጀመር እንዳለበን ነው። ወደ አንድ መጥተን ስምምነት ማድረጋችን የማይቀር ነው" ሲሉ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ለምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። ራማፎሳ እርስ ብርስ በተሳሳረው በዛሬው ዓለም ውስጥ ሀገራት የማይስማሙባቸው ነገሮች ቢኖሩ እንኳን "ችግሮቻቸውን ቁጭ ብለው መፍታት" ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ እና የትብብር ሚኒስትር ሮናልድ ላሞላ አሜሪካ ለሀገራቸው የምትሰጠውን ዕርዳታ ካቆመች በኋላ፤ ደቡብ አፍሪካ ለመነጋገር ያደረገችውን ጥረት ችላ ማለቷን ቀደም ሲል ተናግረዋል። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የደቡብ አፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ነጭ ነዋሪዎች ላይ የዘር መድልዎ ያደረገ ነው በሚል ለሀገሪቱ የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ እንዲቆም ትዕዛዝ መስጠታቸው ይታወሳል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0