ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ጋር ተወያይተዋልከሁለቱ መሪዎች ውይይት በኋላ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ መንግሥት በጋራ ባወጡት መግለጫ የተነሱ አንኳር ነጥቦች፦🟠 የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ነበረበት ለመመለስ እየተደረገ ያለው ተከታታይ ጥረት አካል ነው።🟠 መሪዎቹ ለሁለቱ ሀገራት የጋራ ጥቅም ሲባል ትብብራቸውን ለማጠናከር ቁርጠኝ መሆናቸውን መልሰው ያረጋገጡ ሲሆን፤ በህዝቦቻቸው መካከል ያለውን ጥልቅ ታሪካዊ ትስስርና የጋራ ድንበር በመገንዘብ በዲፕሎማሲያዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በማህበራዊ ትብብር ላይ በመስራት መተማመንን ማጎልበት አስፈላጊ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተዋል።🟠 ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ተደጋጋፊ፣ የጋራ እጣ ፈንታና የጋራ ራዕይ ያላቸው በመሆኑ ዘላቂ ልማት፣ ኢኮኖሚያዊ ውህደት እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማረጋገጥ ስትራቴጂካዊ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።🟠 ሁለቱ መሪዎች በአንካራው ስምምነት መሠረት የቴክኒክ ውይይት መጀመሩን በደስታ እንደተቀበሉ ገልፀው ገንቢ ውይይት እና ትብብር ለማድረግ ቁርጠኝ ነን ብለዋል። 🟠 በሶማሊያ ብሔራዊ ጦር እና በኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አዛዦች መካከል የተደረሰው የፀጥታ ትብብር ስምምነት ቀጣናው ወደ መረጋጋት እንዲመለስ ወሳኝ እርምጃ እንደሆነ ገልፀዋል። 🟠 ሀገራቱ የጋራ ጥቅሞችን በማሳደግ፣ ሰላምና ደህንነትን በማስፈን እና ግንኙነታቸውን በማጠናከር ለዜጎቻቸውና ለሰፊው የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ ነን ብለዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ጋር ተወያይተዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ጋር ተወያይተዋል
Sputnik አፍሪካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ጋር ተወያይተዋልከሁለቱ መሪዎች ውይይት በኋላ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ መንግሥት በጋራ ባወጡት መግለጫ የተነሱ አንኳር ነጥቦች፦🟠 የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት... 27.02.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-02-27T16:11+0300
2025-02-27T16:11+0300
2025-02-27T16:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ጋር ተወያይተዋል
16:11 27.02.2025 (የተሻሻለ: 16:44 27.02.2025)
ሰብስክራይብ