ኬንያ እና ሶማሊያ የንግድ ልውውጣቸውን የሚገድቡ መሰናክሎችን ለማስወገድ የሚያስችል ስምምነት ለማድረግ ወይይት ላይ መሆናቸው ተጠቆመ

ሰብስክራይብ
ኬንያ እና ሶማሊያ የንግድ ልውውጣቸውን የሚገድቡ መሰናክሎችን ለማስወገድ የሚያስችል ስምምነት ለማድረግ ወይይት ላይ መሆናቸው ተጠቆመየሁለቱን ሀገራት የንግድ ትብብር ለማሳደግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሞ ወደ ስራ መግባት፤ የተሳለጠ የንግድ ግንኙነትን ለማመቻቸት ወሳኝ እርምጃ መሆኑን በሶማሊያ-ኬንያ የንግድ ሳምንት ላይ የተገኙት የኬንያ የንግድ ምክር ቤት ፀሃፊ ሊ ኪንያንጁዪ ተናግረዋል።የንግድ ልውውጣቸውን በሚገድቡ መሰናክሎች ላይ ለመወያየት የጋራ የንግድ ኮሜቴ ማቋቋም እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።የሶማሊያ ኢኮኖሚ እያደገ እንደመጣ እና ሀገሪቱ በግብርና፣ በአሳ ምርት፣ በማኑፋክቸሪንግ እና በመሠረተ ልማት እምቅ አቅም እንዳላት አፅንኦት የሰጡት የኔሽን ሚዲያ ግሩፕ ሊቀመንበር ዊልፍሬድ ኪቦሮ፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ ሊያድግ ይገባል ብለዋል። ኪቦሮ የሶማሊያን ትልቅ የአሳ ምርት ዘርፍና የባህር ላይ ንግድ የሚደግፈውን ሰፊ የባህር ዳርቻ በማሳያነት አንስተዋል።ሊ ኪንያንጁዪ በበኩላቸው ሶማሊያ እና ኬንያ የድንበር ደህንነት እና ንግድን ማሳለጥ ላይ፣ የጉሙሩክ ስራዎችን ማሻሻል እና የንግድ ቁጥጥሮችን ማዘመን ላይ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0